ሚድዌስት የኢትዮጵያ ወንጌላዊ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት
የመጀመሪያ ስብሰባውን ከሦስት አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕመናንና መሪዎቻቸው በተገኙበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 ዓ,ም, በሂውስተን ከተማ ላይ አደረገ። በዚህ ስብሰባ ላይ ተካፋይ የነበሩት ሦስት አብያተ ክርስቲያናት በካንሳስ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስቲያን ፣ በሂውስተን የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስቲያንና ፣ በዳላስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርስቲያን ናቸው።
ይህ ስብሰባ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዓመት አንድ ጊዜ ለአራት ተከታታይ ቀናት ለአባላቱ አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ ሲካሄድ ከቆየ በኋላ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በኦክላሆማ ግዛት በዴቪስ ከተማ Falls Creek Baptist Conference Center እየተካሄደ ይገኛል።
ስብሰባው መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ የኅብረቱን አባልነት ያገኙ የአብያተ ክርስቲያናት ቁጥር ከሦስት ወደ ስምንት የጨመረ ሲሆን የተካፈይ ምዕመኑም ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት ትልቅ ዕድገት አሳይቷል።
የስብሰባው ይዘትና ጥራት ፤ አዘገጃጀቱና አቀራረቡ በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ምዕመናን በየፈርጁ የሚያካትት ሲሆን መንፈሳዊ ሕይወትን በማነፅ ፣ ወገኖችን በክርስቶስ ፍቅር በማቀራረብና በማስተሳሰር በምዕመናኑ ልብ ውስጥ ዘወትር የሚታወስ ልዩ ጊዜን ያመቻቸ ስብሰባ መሆኑ በግልፅ የሚታይ ነው።
These are the published rates for boarding and food for the
2011 Midwest Ethiopian Evangelical Churches annual conference.
$ 135 ( Adults)
$ 80 (Ages 3-12)
$ 20 (Under 3)
The people who come but do not board at the center need to pay for each meal
that they eat.
$6.25 for breakfast
$7.25 for lunch
$7.25 for dinner
They will also need to pay a registration fee of $6.00 per person/ per day.